145 ሚሊየን ብር ይወጣበት የነበረ ቦይለር በራስ አቅም ተጠገነ

በፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ 145 ሚለየን ብር ለጥገና የተጠየቀበት ቦይለር በራስ አቅም ተጠገነ፡፡ በፈንጫኣ እና በመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች ከፍተኛ የቦይለር ባለሙያዎች የተጠገነው የፋብሪካው ቦይለር ቁጥር 3 የጥገና ጨረታ ወጥቶበት የነበረ ሲሆን፣ በወቅቱ ተጫራቾች ያቀረቡት ዋጋ ከፍተኛ በመሆኑ እና ለጥገና የጠየቁት ጊዜም በመርዘሙ የፋብሪካው ማኔጅመንት የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ እና የመተሐራ ስካር ፋብሪካ የቦይለር ባለሙያዎች እንዲጠግኑት ውሳኔ አሳልፎ እንደነበር የፊንጫኣ ፋብሪካ የሕዝብ ግንኙነት ክፍል በላከልን መረጃ አስታውሷል፡፡ በዚህ መሰረት የሁለቱ ፋብሪካዎች የቦይለር ባለሙያዎች ከጥቅምት 30 ጀምሮ ለ40 ቀናት ባደረጉት ርብርብ የጥገና ሥራው ታህሣስ 10/2012 ዓ.ም ተጠናቆ ቦይለሩ የኃይል ምርት እንዲጀምር ተደርጓል፡፡ ከ50 በላይ…

የስኳር ኢንደስትሪውን ወደ ለውጥ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚቻል ተገለጸ

ዘንድሮ በዝግጅት ምዕራፍ የታየው የስኳር ፋብሪካዎች የክረምት ጥገና አፈጻጸም በታቀደው የምርት መጠን ከታገዘ ኢንደስትሪውን ወደ ለውጥ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚቻል እምነታቸው መሆኑን የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ገለጹ፡፡ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ ገብረመስቀል ይህንን የተናገሩት በኮርፖሬሽኑ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ዛሬ ታህሳስ 1/2012 ዓ.ም. ተገኝተው በሰጡት የሥራ መመሪያ ነው፡፡ ፋብሪካዎች የክረምት ጥገና አጠናቀው በተያዘላቸው ጊዜ ወደ ምርት መግባታቸው በቀጣይ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ትልቅ አቅም እንዳለ አመላካች ነው ብለዋል፡፡ የስኳር ኢንደስትሪው ዕድገትም ሆነ ወድቀት በተቋሙ አመራር እጅ ነው…

የኮርፖሬሽኑ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው

የስኳር ፋብሪካዎች የክረምት ጥገና የዝግጅት ምዕራፍን ያካተተ የኮርፖሬሽኑ አጠቃላይ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም እየተገመገመ ነው፡፡ የዋናው መስሪያ ቤት፣ የስኳር ፋብሪካዎች፣ የፕሮጀክቶችና የመሰረታዊ የሰራተኛ ማኅበር አመራሮች በተገኙበት ዛሬ ህዳር 30/ 2012 ዓ.ም የተጀመረው ግምገማ ለቀጣይ ሦስት ቀናት ይቆያል፡፡ የኮፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ መድረኩን ሲከፍቱ ፋብሪካዎች የአመቱን እቅድ በማሳካት በገቢ ድርሻቸው መተዳደር እንዳለባቸው ተናግረዋል፡፡ በመቀጠልም የተቋሙ የአምስት ወራት የዕቅድ አፈጻጸምና የሪፎርም ሥራዎች ክትትል ሪፖርት በአቶ ሳምሶን ወልቀባ የኮርፖሬት ፕላኒንግ ሥራ አስፈጻሚ ቀርቧል፡፡ በዛሬው የግማሽ ቀን ውሎ የወንጂ ሸዋ፣ የመተሐራ እና የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካዎች ዋና ሥራ አስኪያጆች አጠር ያለ ተጨማሪ…

ስድስት የስኳር ፋብሪካዎች ከወራት በኋላ ወደግል ይዞራሉ

አዲስ አበባ ፣ ህዳር 17 ፣ 2012 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስቴር ስድስት የስኳር ፋብሪካዎች ከወራት በኋላ ወደ ግል እንደሚዞሩ አስታወቀ። ሚኒስቴሩ በኢትዮጵያ የስኳር ኢንዱስትሪ ማሻሻያ ላይ ትኩረት የሚያደርግ የውይይት መድረክ ይፋ አድርጓል። የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታው ዶክተር እዮብ ተካልኝ በጉዳዩ ዙሪያ በሰጡት መግለጫ፥ አሁን ላይ በመንግስት ስር ያሉ 13 የስኳር ፋብሪካዎች የቴክኒክ፣ የዋጋ፣ የማህበራዊና የአካባቢ ጥበቃ ጥናቶች እየተከናወነላቸው ይገኛል ብለዋል። ጥናቱ በመጭው ታህሳስ ወር ይጠናቀቃል ያሉት ሚኒስትር ዲኤታው፥ ከዚህ ውስጥ ስድስቱ ወደግሉ እንደሚዞሩ ተናግረዋል። ከዚህ አንጻርም ከገዥዎች የማዞር ሂደቱን መጀመር በሚያስችል መልኩ ጠቃሚ ግብዓት መሰብሰቡንም አስረድተዋል። ሚኒስቴሩ ግልጽና ሁሉን አሳታፊ…

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕከት

በዓለም ገበያ ከፍተኛ ተፈላጊነት ካላቸው 10 የግብርና ምርቶች ወይም ሸቀጦች ውስጥ አንዱ ስኳር ነው፡፡ ለዚህ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ኢትዮጵያ ተስማሚ የሆነ እምቅ የተፈጥሮ ሃብትና ለሥራ ዝግጁ የሆነ የሰው ኃይል አላት፡፡ ለሸንኮራ አገዳ ካላት ምቹ የተፈጥሮ ፀጋ አኳያም በአገዳ ምርታማነት በአለምአቀፍ ደረጃ ከሚታወቁ ጥቂት ሀገራት ተርታ በግንባር ቀደምነት ተሰልፋለች፡፡ ይህንን ሃብት ከግምት ውስጥ ያስገባው የኢፌዲሪ መንግሥት የስኳር ኢንደስትሪ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ውስጥ የመሪነት ሚና እንዲጫወት ለዘርፉ ከፍተኛ የኢንቨስትመንት ካፒታል በመመደብ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ማካሄድ ከጀመረ ዘጠኝ አመታት ተቆጥረዋል፡፡ ምንም እንኳ በዘርፉ ከተቀመጡ ግቦች አንጻር በእስካሁኑ የልማት ጥረት የተገኘው ውጤት የተጠበቀውን ያህል ባይሆንም…

በስኳር ኮርፖሬሽን አማካይነት እየተካሄደ የሚገኝ የስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የአክስዮን ሽያጭ አለመኖሩ ተገለጸ

የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ጋሻው አይችሉህም

በአሁኑ ወቅት በመንግሥትም ሆነ በስኳር ኮርፖሬሽን አማካይነት እየተካሄደ የሚገኝ የስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች የአክስዮን ሽያጭ አለመኖሩን በስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ አቶ ጋሻው አይችሉህም በተለይ ለኢቲቪ ገልጸዋል። የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች እና ፋብሪካዎችን በሙሉ ወይም በከፊል ወደ ግል ይዞታ ለማዘዋወር መንግስት ያሳለፈውን ውሳኔ ተከትሎ የገንዘብ ሚኒስቴር በስኳር ኢንዱስትሪው ላይ ለባለሃብቶች እና ኩባንያዎች የመረጃ ጥያቄ አቅርበው በርካቶች በዘርፉ ለመሰማራት ፍላጎታቸውን እየገለጹ መሆናቸው ይታወቃል። ከዚህ ጋር በተያያዘ መንግሥት ወይም ስኳር ኮርፖሬሽን ከሚያስተዳድራቸው 13 የስኳር ፋብሪካዎች እና ፕሮጀክቶች ውስጥ ተጨማሪ የኢንቨስትመንት ካፒታል የሚጠይቁ እና በግንባታ ላይ የሚገኙ ስድስት ፋብሪካዎች /ፕሮጀክቶች/ በ2012 ዓ.ም ወደ…

የፕላንት እና ፕሮሰስ ጉባኤ ተካሄደ

ላለፉት ዘጠኝ ዓመታት ተቋርጦ የቆየው የፕላንት እና ፕሮሰስ ጉባኤ /Plant & Process Conference በአዳማ ከተማ በኤክስኪዩቲቭ ሆቴል ከሐምሌ 18-19/2011 ዓ.ም. ድረስ ተካሂዷል፡፡ ለሁለት ቀናት በተካሄደው በዚህ ጉባኤ 227 ተሳታፊዎች የተገኙ ሲሆን፣ የ10 ዓመታት የሸንኮራ አገዳ ልማትና የፋብሪካ የምርትና ምርታማነት አፈጻጸምን የሚያሳዩ ጽሁፎች በፕረዘንቴሽን መልክ ቀርበው መፍትሔ አመላካች ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር የሸንኮራ አገዳ ልማት የአምስት ዓመት እንዲሁም የፋብሪካ የሦስት ዓመት ፍኖተ ካርታዎች ለውይይት ቀርበው አስተያያት ተሰጥቶባቸዋል፡፡ በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ጉባኤው የተዘነጉ መልካም አሠራሮችንና ወደ ስኬት የሚያሸጋግሩንን የሥራ ባህሎች የምንመልስበት…

የስኳር ኮርፖሬሽን ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን የራሳቸውን አሻራ አኖሩ

በሀገር አቀፍ ደረጃ “የአረንጓዴ አሻራ ቀን” በሚል መሪ ቃል ሁለት መቶ ሚሊየን ችግኞች ለመትከል የተካሄደውን ሕዝባዊ ንቅናቄ ተከትሎ የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባን ጨምሮ የዋናው መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች እንዲሁም የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች ዋና ሥራ አስኪያጆች የካ ሚሊኒየም ፓርክ አካባቢ በሚገኘው የደን ክልል ዛሬ ሐምሌ 22/2011 ዓ.ም. የጽድ፣ የግራር እና ሌሎች ሀገር በቀል እጽዋት ችግኞችን ተክለዋል፡፡ የተቋሙ ሠራተኞች አንድ ላይ በመሆን ችግኞችን ሲተክሉ የዛሬው ለስድስተኛ ጊዜ ሲሆን፣ ከዚህ ቀደም ለአምስት ጊዜያት ያህል በየካና ፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢዎች በሚገኙ የደን ክልሎች ችግኞችን ተክለዋል፡፡ ኮርፖሬሽኑ በየዓመቱ በችግኝ ተከላ እየተሳተፉ ካሉ…

በምርምር የተገኙ አራት ሀገር በቀል የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች እውቅና አገኙ

በስኳር ኮርፖሬሽን በምርምርና ልማት ዋና ማዕከል አማካይነት በከፍተኛ ተመራማሪ ዶ/ር ኢሳያስ ጠና ጋሻው በምርምር የተገኙ አራት ሀገር በቀል የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች በሀገራችን የስኳር ኢንደስትሪ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በብሔራዊ ዝርያ አጽዳቂ ኮሚቴ ግንቦት 23/2011 ዓ.ም. እውቅና አግኝተው ተመዝግበዋል፡፡ ዝርያዎቹ ካላቸው በርካታ ከፍተኛ ጠቀሜታ ውስጥ የሚከተሉት በዋነኛነት ይጠቀሳሉ፡፡ ለተለያዩ ሸንኮራ አገዳ አብቃይ ሥነ ምህዳሮች ተስማሚ መሆናቸው፣ ከፍተኛ የአገዳ ምርትና የስኳር ይዘት ያላቸው መሆኑ (ከነባር ዝርያዎች በተሻለ ሁኔታ ከ20-30 በመቶ አብላጫ ከፍተኛ የስኳር ምርት መስጠት ይችላሉ)፣ ነባር የሸንኮራ አገዳ ዝርያዎች ለአጨዳ ከሚወስድባቸው ረጅም ጊዜ (ከ18-22 ወራት) ጋር ሲነጻጸር የተሻሻሉት ዝርያዎች ከ13-14 ወራት ጊዜ…

የስኳር ልማት ዘርፍን ካለበት ችግር ለማላቀቅ የድርሻውን ኃላፊነት እንደሚወጣ የስኳር ኮርፖሬሽን ሥራ አመራር ቦርድ ገለጸ

አዲስ የተሾሙት የቦርድ ሰብሳቢና ሌሎች ሦስት አባላት ከተቋሙ ማኔጅመንት ጋር ተዋውቀዋል የስኳር ልማት ዘርፍን ካለበት ችግር በማውጣት ኢንዱስትሪው ለሀገሪቱ ኢኮኖሚ እድገት የሚጠበቅበትን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት የበኩሉን ድርሻ እንደሚወጣ በአዲስ መልክ የተሰየመው የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ገለጸ፡፡ ቦርዱ በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሰኔ 13/2011 ዓ.ም. ባካሄደው ስብሰባ ኢንደስትሪውን ካለበት ችግር ለማላቀቅና በዘርፉ የታለሙትን ግቦች ለማሳካት አዲስ ስትራተጂ በፍጥነት ነድፎ ተግባራዊ ማድረግ ይገባል ብሏል፡፡ የእለቱን ስብሰባ የመሩት አቶ በየነ ገብረመስቀል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር እና የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ እራሳቸውን እና ሌሎች ሦስት አዳዲስ የቦርድ አባላትን ካስተዋወቁ…