ስኳር ኮርፖሬሽን 100 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን በእርዳታ አገኘ

ስኳር ኮርፖሬሽን 100 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን/Face masks የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካን ከሚገነባው የቻይናው JIEC ኩባንያ (Jiang Lian International Engineering Company) በእርዳታ አገኘ፡፡

በእርዳታ የተገኙትን ጭምብሎች ለስኳር ፋብሪካዎች፣ ፕሮጀክቶችና ለኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ማከፋፈል ተጀምሯል፡፡

ይህም እርዳታ በስኳር ኢንደስትሪ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት ያግዛል፡፡

Related posts