የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን የራሳቸውን አሻራ አኖሩ

ችግኞችን ሲተክሉ የዘንድሮው ለሰባተኛ ጊዜ ነው
 
የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባን ጨምሮ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ ሰኔ 10/2012 ዓ.ም. የጽድ፣ የግራር፣ የወይራ፣ የብሳና፣ የዋንዛ እና ሌሎች የሀገር በቀል እጽዋት ችግኞችን ለሰባተኛ ጊዜ ተክለዋል፡፡
 
በቀጣይም ችግኞቹ እስኪጸድቁ ድረስ የእንክብካቤ ሥራውን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡
 
የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሚገኙ ጥብቅ የደን ክልሎች ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴ ልማት እና አካባቢ ጥበቃ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ናቸው፡፡

Related posts