የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተጀመረ

አገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና አመራሮች ግንቦት 28/2012 ዓ.ም የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡

የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልአዚዝ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት የችግኝ ተከላ ለአረንጓዴ ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ችግኝ ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቅ መንከባከብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚደረገው ጥንቃቄ ጋር ተጣጥሞ እንዲካሄድም አስገንዝበዋል፡፡

በእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ የአገዳ ተከላና እንክብካቤ መመሪያ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ወርቅነህ አሠፋ በበኩላቸው በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ቀን መርሃ ግብር በፋብሪካው ከ15 ሺህ በላይ ችግኝ ለመትከል እቅድ መያዙንና ለዚህም የሚሆን በቂ ችግኝ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡ ከሚተከሉት ችግኞች ውስጥም ለምግብነት የሚውሉና ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ያላቸው ተክሎች እንደሚገኙበት አክለው ተናግረዋል፡፡

Related posts