ስኳርን ከኦሞ ገነት…

ለተነሳበት ሀገር ምንም አይነት ጥቅም ሳይሰጥ ለዘመናት ለም አፈር ተሸክሞ ወደ ጎረቤት ሀገር ይጋልብ የነበረው የኦሞ ወንዝ ዛሬ ላይ በኢትዮጵያውያን ተገርቶ ለስኳር ምርት ወሳኝ ሃብት በመሆን እያገለገለ ይገኛል፡፡ በቅርቡ ለተመረቀው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሦስት እና ለቁጥር ሁለት ስኳር ፋብሪካዎች ግብዓት የሚውል አገዳን በማልማትም አጋርነቱን አስመስክሯል፡፡ ዛሬ በዚህች መጣጥፍ ለመተረክ የፈለግነው ስለኦሞ ወንዝ ሳይሆን ይልቁንም ወንዙን ተገን አድርጎ ስለተገነባው የኦሞ ኩራዝ ቁጥር ሦስት ስኳር ፋብሪካ ይሆናል፡፡ በቅድሚያ ግን የስኳር ኢንዱስትሪ በኢትዮጵያ እንዴት እንደተጀመረ በምናብ ልናስቃኛችሁ ስለወደድን ከዛሬ 65 ዓመት በፊት የነበረውን ታሪክ እነሆ ከብዙ በጥቂቱ አቅርበናል፡፡ በተፈጥሮ ሀብቶቻቸው የቋመጡባቸውን፣ በፀጋዎቻቸው የጎመዡባቸውን…