ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ ያለው ኢንዱስትሪ

የሀገራችን ኢንዱስትሪ በኢኮኖሚው ውስጥየመሪነቱን ሚና እንዲጫወት የላቀ አስተዋጽኦካላቸው ትላልቅ ፕሮጀክቶች መካከል አንዱየስኳር ልማት ፕሮጀክት ነው። ኢትዮጵያ ይህንኤክስፖርት መር የሆነ የማኑፋክቸሪንግኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማስፋፋትና ምርታማነቱንለማሳደግ የሚያስችል ከፍተኛ የሰው ኃይልናየተፈጥሮ ሃብት አላት፡፡ በተለይም ሀገሪቱ ለሸንኮራ አገዳ ልማት ተስማሚአየር ንብረት፣ በመሰኖ ሊለማ የሚችል ሰፊየእርሻ መሬት (ከ500ሺ ሄክታር በላይ) እንዲሁም በቂ ውሃ ያላት በመሆኑ ዘርፉ የበለጠትኩረት እንዲሰጠው ተደርጓል፡፡ ከዚህ ባሻገር መንግሥት የሀገሪቱ ህዝቦች ፍትሃዊ የልማት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በሚከተለው የፖሊሲአቅጣጫ መሰረት በወንጂ ሸዋና መተሓራ ስኳር ፋብሪካዎች ብቻ ለረጅም ዓመታት ያህል ተወስኖ የቆየውን የስኳር ኢንዱስትሪበተለይም ከ2003ዓ.ም ወዲህ በኦሮሚያ፣ በአፋር፣ በአማራ እና በትግራይ ክልሎች እያስፋፋ ይገኛል፡፡ በርካታ ጠቀሜታዎች…

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ስኬታማ ጉዞ

መግቢያ የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን የሰላማጎና የኛንጋቶም ወረዳዎችን፣ በቤንች ማጂ ዞን የሱርማና የሚኤኒትሻሻ ወረዳዎችን እንዲሁም በከፋ ዞን የዴቻ ወረዳ አንዳንድ የተመረጡ ቦታዎችን ያካተተ ነው። 1.1 ለስኳር ልማቱ የተመረጠው አካባቢ ሁኔታ በተከለሰው የስኳር ልማት ዘርፍ ዕቅድ መሰረት በቀን እያንዳንዳቸው 12,000 ቶን አገዳ መፍጨት የሚችሉ ሶስት ስኳር ፋብሪካዎችና በቀን 24,000 ቶን አገዳ መፍጨት የሚችል አንድ ስኳር ፋብሪካ እየተገነባበት የሚገኘው ይህ ፕሮጀክት ለአራቱም ፋብሪካዎች በግብዓትነት የሚውል የሸንኮራ አገዳ በ100,000 ሄክታር መሬት ላይ እየለማ ይገኛል፡፡ ፕሮጀክቱ የሚገኝበት አካባቢ ስፍራ ለኬንያ ድንበር ቅርብ ከመሆኑ የተነሳ ኢትዮጵያ…