ምርምርና ልማት ዋና ማዕከል

በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ሥራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአምስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡ ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር እ.ኤ.አ. ከ1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ሥልጠና ይሰጥ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ኋላ ላይ የፋብሪካዎቹን ወደ መንግሥት ይዞታነት መሸጋገር ተከትሎ የምርምር ሥራው በተለያዩ አደረጃጀቶች ሲመራ ቆይቶ የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 192/2003 ሲቋቋም ለምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የማምረቻ ወጪን መቀነስ የሚያስችል እንዲሁም ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ ምርምር (applied…