የስኳር ኢንደስትሪውን ወደ ለውጥ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚቻል ተገለጸ

ዘንድሮ በዝግጅት ምዕራፍ የታየው የስኳር ፋብሪካዎች የክረምት ጥገና አፈጻጸም በታቀደው የምርት መጠን ከታገዘ ኢንደስትሪውን ወደ ለውጥ ምዕራፍ ማሸጋገር እንደሚቻል እምነታቸው መሆኑን የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ገለጹ፡፡ የመንግስት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና የኮርፖሬሽኑ የቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ ገብረመስቀል ይህንን የተናገሩት በኮርፖሬሽኑ የአምስት ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ መድረክ ላይ ዛሬ ታህሳስ 1/2012 ዓ.ም. ተገኝተው በሰጡት የሥራ መመሪያ ነው፡፡ ፋብሪካዎች የክረምት ጥገና አጠናቀው በተያዘላቸው ጊዜ ወደ ምርት መግባታቸው በቀጣይ በዘርፉ የተሻለ ውጤት ለማምጣት ትልቅ አቅም እንዳለ አመላካች ነው ብለዋል፡፡ የስኳር ኢንደስትሪው ዕድገትም ሆነ ወድቀት በተቋሙ አመራር እጅ ነው…