የጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ መጪው ግንቦት ወር የሙከራ ምርት እንደሚጀምር ተገለጸ

* ፕሮጀክቱ በባለድርሻ አካላትና በብዙሃን መገናኛ ጋዜጠኞች ተጎብኝቷል የጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ በመጪው ግንቦት ወር የሙከራ ምርት እንደሚጀምር የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ገለጹ፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ይህን ያስታወቁት ኮርፖሬሽኑ በበለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ለባለድርሻ አካላትና ለመገናኛ ብዙሃን ጥር 15 እና 16/2012 ዓ.ም. ባዘጋጀው የጉብኝት መርሃ ግብር ላይ ነው፡፡ በጉብኝቱ ወቅት ከኮርፖሬሽኑ የሥራ አመራር ቦርድ፣ ከገንዘብ ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት፣ ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ እንዲሁም የፕሮጀክቱ አጎራባች ከሆኑ ሦስት ወረዳዎች የተውጣጡ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች እና ከአዲስ አበባና ከአማራ ክልል የመጡ ጋዜጠኞች ተሳትፈዋል፡፡ በግንባታ…