ለንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማዘጋጃ የሚያገለግል ከ3 ሚሊዮን ሊትር በላይ ቴክኒካል አልክሆል አለ

ለንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ማዘጋጃ የሚያገለግል ከ3 ሚሊዮን ሊትር በላይ ቴክኒካል አልክሆል በፊንጫአ እና በመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎች ይገኛል፡፡ ፋብሪካዎቹ በቀን 100 ሺህ ሊትር የሚጠጋ ቴክኒካል አልክሆል በማምረት ላይ ናቸው፡፡ በአሁኑ ወቅት በአለም ደረጃ የተከሰተውን የኮሮና ቫይረስ/COVID 19 ወረርሽኝ ሥርጭትን ለመከላከል የሚያገለግሉ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ለማዘጋጀት በግብዓትነት የሚውለውን  ቴክኒካል አልክሆል የምርት መጠን ለማሳደግ ስኳር ኮርፖሬሽን ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ በቂ ቴክኒካል አልክሆል በመኖሩም በተፈቀደላቸው ኮታ መሰረት ምርቱን እየወሰዱ ከሚገኙ ፋርማሲዎችና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁስ አምራች ፋብሪካዎችና ድርጅቶች በተጨማሪ ስኳር ኮርፖሬሽን ከንግድና ኢንደስትሪ ሚኒስቴር እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመነጋገር ተጨማሪ ሰባት አዳዲስ ድርጅቶች ቴክኒካል…

የኮርኖ ቫይረስ ሥርጭትን የሚከላከልና የሚቆጣጠር ስትሪንግ ኮሚቴ ሥራ ጀመረ

በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ሥርጭትን የሚከላከልና የሚቆጣጠር ስትሪንግ ኮሚቴ ከመጋቢት 8/2012 ዓ.ም አንስቶ ሥራ ጀመረ፡፡ በኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የበላይ ጠባቂነት እና በኮርፖሬት ሰርቪስ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሰብሳቢነት የሚመራው ይህ ኮሚቴ ከፋብሪካ ኦፕሬሽን፣ ከእርሻ ኦፕሬሽንና ከፋይናንስ ዘርፎች ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚዎች እንዲሁም ከዋና ሥራ አስፈጻሚ አማካሪ፣ ከኮሚዩኒኬሽንና ከጤና አገልግሎት ኃላፊዎች በተውጣጡ ስድስት አባላትና ጸኃፊ የተዋቀረ ነው፡፡ ኮሚቴው የተሰጠውን ተልዕኮ ለመፈጸም ዝርዝር ተግባርና ኃላፊነት እንዲሁም የድርጊት መርሃ ግብር አዘጋጅቶ ወደ ሥራ ከመግባቱ ባሻገር የመረጃ ልውውጥን ለማሳለጥ፣ ግንዛቤን ለመፍጠር፣ ቁሳቁሶችን በሚፈለገው ደረጃ ለማቅረብ እንዲሁም የክትትልና ቁጥጥር…