የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተጀመረ

አገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና አመራሮች ግንቦት 28/2012 ዓ.ም የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልአዚዝ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት የችግኝ ተከላ ለአረንጓዴ ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ችግኝ ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቅ መንከባከብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚደረገው ጥንቃቄ ጋር ተጣጥሞ እንዲካሄድም አስገንዝበዋል፡፡ በእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ የአገዳ ተከላና እንክብካቤ መመሪያ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ወርቅነህ አሠፋ በበኩላቸው በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ቀን መርሃ ግብር በፋብሪካው ከ15 ሺህ በላይ ችግኝ ለመትከል…

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የከሰምና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ጎበኘ

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የከሰምና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንቦት 13/2012 ዓ.ም በመጎብኘት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ፡፡ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና በስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ ገብረመስቀል በተመራው በዚህ ጉብኝትና ውይይት ላይ የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐብታሙ ኃ/ሚካኤል እና የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ተገኝተዋል፡፡ በወቅቱ በፋብሪካዎቹ ከተካሄደው የመስክ ምልከታ በተጨማሪ የተቋማቱ የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የምርትና ምርታማነት ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ለምርትና ምርታማነት ማነቆ የሆኑ የፋብሪካ ክፍሎች የመለዋወጫ እጥረትና…