የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን የራሳቸውን አሻራ አኖሩ

ችግኞችን ሲተክሉ የዘንድሮው ለሰባተኛ ጊዜ ነው   የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባን ጨምሮ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ ሰኔ 10/2012 ዓ.ም. የጽድ፣ የግራር፣ የወይራ፣ የብሳና፣ የዋንዛ እና ሌሎች የሀገር በቀል እጽዋት ችግኞችን ለሰባተኛ ጊዜ ተክለዋል፡፡   በቀጣይም ችግኞቹ እስኪጸድቁ ድረስ የእንክብካቤ ሥራውን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡   የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሚገኙ ጥብቅ የደን ክልሎች ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴ ልማት እና አካባቢ ጥበቃ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ናቸው፡፡

በክረምት ወቅት የስኳር ፍላጎት አቅርቦትን ለማሟላት 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ለመጠባበቂያ እየተከማቸ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በክረምት ወቅት የስኳር ፍላጎት አቅርቦትን ለማሟላት 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ለመጠባበቂያ እየተከማቸ መሆኑ ተገለጸ። የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ከፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ በተያዘው የ2012 ዓ.ም የክረምት ወቅት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ጥገና መግባትን ተከትሎ እስከ 2013 ጥቅምት ወር በሀገሪቱ የስኳር እጥረት እንዳያጋጥም ዝግጀት መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም በሀገር ውስጥ የተመረተ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በመጋዘን የሚገኝ ሲሆን÷ 2 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ደግሞ ከውጭ ሀገር በመግዛት በቅርቡ ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል። በክርምት ወራት ፋብሪካዎች…