«የስኳር ፕሮጀክቶች እየሰራን እንማራለን በሚል ድፍረት እና ያለ በቂ ገንዘብ መጀመራቸው እንዳይሳኩ አድርጓቸዋል»- አቶ ጋሻው አይችሉህም የስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ

 አዲስ አበባ፡- የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች «እየሰራን እንማራለን» በሚል ድፍረትና በቂ የገንዘብ አቅም በሌለበት መጀመራቸው ላለመሳካታቸው ምክንያት እንደሆነ የስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ። ሥራ አስፈፃሚው አቶ ጋሻው አይችሉህም በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት፤ ፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅም ሆነ መሳካት ያልቻሉት ሲቋቋሙ በቂ የአዋጭነት ጥናት አለመጠናቱ፤ በቂ የገንዘብ አቅም በሌለበት ሁኔታ መጀመራቸው እና ለፋብሪካዎቹ የተመረጡት አካባቢዎች ቆላማ እና ምንም ዓይነት መሠረተ ልማት የሌለባቸው በመሆናቸው ነው። በተጨማሪም የወሰን ማስከበር ችግር፤ ሥራውን የወሰደው ኮንትራክተርም በቂ ልምድ ሳይኖረው «እየሰራን እንማራለን» ብሎ በድፍረት ብቻ ያለ በቂ እውቀት ሥራውን መጀመሩ ለፕሮጀክቶቹ አለመሳካት ዋንኛ ተግዳሮቶች እንደነበር…