የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን የራሳቸውን አሻራ አኖሩ

ችግኞችን ሲተክሉ የዘንድሮው ለሰባተኛ ጊዜ ነው   የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባን ጨምሮ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ ሰኔ 10/2012 ዓ.ም. የጽድ፣ የግራር፣ የወይራ፣ የብሳና፣ የዋንዛ እና ሌሎች የሀገር በቀል እጽዋት ችግኞችን ለሰባተኛ ጊዜ ተክለዋል፡፡   በቀጣይም ችግኞቹ እስኪጸድቁ ድረስ የእንክብካቤ ሥራውን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡   የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሚገኙ ጥብቅ የደን ክልሎች ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴ ልማት እና አካባቢ ጥበቃ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ናቸው፡፡

በክረምት ወቅት የስኳር ፍላጎት አቅርቦትን ለማሟላት 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ለመጠባበቂያ እየተከማቸ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በክረምት ወቅት የስኳር ፍላጎት አቅርቦትን ለማሟላት 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ለመጠባበቂያ እየተከማቸ መሆኑ ተገለጸ። የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ከፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ በተያዘው የ2012 ዓ.ም የክረምት ወቅት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ጥገና መግባትን ተከትሎ እስከ 2013 ጥቅምት ወር በሀገሪቱ የስኳር እጥረት እንዳያጋጥም ዝግጀት መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም በሀገር ውስጥ የተመረተ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በመጋዘን የሚገኝ ሲሆን÷ 2 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ደግሞ ከውጭ ሀገር በመግዛት በቅርቡ ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል። በክርምት ወራት ፋብሪካዎች…

የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተጀመረ

አገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና አመራሮች ግንቦት 28/2012 ዓ.ም የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልአዚዝ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት የችግኝ ተከላ ለአረንጓዴ ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ችግኝ ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቅ መንከባከብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚደረገው ጥንቃቄ ጋር ተጣጥሞ እንዲካሄድም አስገንዝበዋል፡፡ በእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ የአገዳ ተከላና እንክብካቤ መመሪያ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ወርቅነህ አሠፋ በበኩላቸው በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ቀን መርሃ ግብር በፋብሪካው ከ15 ሺህ በላይ ችግኝ ለመትከል…

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የከሰምና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ጎበኘ

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የከሰምና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንቦት 13/2012 ዓ.ም በመጎብኘት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ፡፡ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና በስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ ገብረመስቀል በተመራው በዚህ ጉብኝትና ውይይት ላይ የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐብታሙ ኃ/ሚካኤል እና የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ተገኝተዋል፡፡ በወቅቱ በፋብሪካዎቹ ከተካሄደው የመስክ ምልከታ በተጨማሪ የተቋማቱ የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የምርትና ምርታማነት ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ለምርትና ምርታማነት ማነቆ የሆኑ የፋብሪካ ክፍሎች የመለዋወጫ እጥረትና…

በነባር ስኳር ፋብሪካዎች የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ በኮሮና ቫይረስ መከላከልና በቀጣይ ሥራዎች ዙሪያ በቪድዮ ኮንፈረንስ ውይይት ተካሄደ

በወንጂ ሸዋ፣ በመተሐራና በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የፋብሪካ የክረምት ጥገናና የዝግጅት ምዕራፍ ዕቅድ እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙሪያ ግንቦት 4/2012 ዓ.ም በቪድዮ ኮንፈረንስ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ በተመራው በዚህ ውይይት ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት አመራሮች እንዲሁም የሦስቱም ስኳር ፋብሪካዎች ዋና ሥራ አስኪያጆችና የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት የፋብሪካዎቹ ሦስተኛ ሩብ ዓመት የምርት አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር አበረታች መሆኑን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ይሁንና ከዘንድሮ ዕቅድ አኳያ ሲታይ ግን የሚቀረውን ለማሟላት በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ…

ስኳር ኮርፖሬሽን 100 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን በእርዳታ አገኘ

ስኳር ኮርፖሬሽን 100 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን/Face masks የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካን ከሚገነባው የቻይናው JIEC ኩባንያ (Jiang Lian International Engineering Company) በእርዳታ አገኘ፡፡ በእርዳታ የተገኙትን ጭምብሎች ለስኳር ፋብሪካዎች፣ ፕሮጀክቶችና ለኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ማከፋፈል ተጀምሯል፡፡ ይህም እርዳታ በስኳር ኢንደስትሪ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት ያግዛል፡፡

በስኳር ኢንደስትሪ የኮሮና ቫይረስን/COVID-19 ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል

በስኳር ኢንደስትሪ የኮሮና ቫይረስ በሽታን/COVID-19 ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በተቋቋሙ አብይና የቴክኒክ ኮሚቴዎች መሪነት ወረርሽኙን ለመከላከል ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም በርካታ ሠራተኞች በሚገኙባቸው የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የቫይረሱን ሥርጭት በተቀናጀ ሁኔታ ለመከላከል እንዲቻል በአካባቢዎቹ ከሚገኙ ማኅበረሰቦች፣ አጋር የልማት ድርጅቶች እንዲሁም ከወረዳ መስተዳድሮች ጋር ጥምረት በመፍጠር ሥራዎችን በጋራ ለመፈጸም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ የጤና ተቋማት ጋር በፈጠረው ግንኙነት ለጤና ባለሙያዎች ሥልጠናዎችን ከማመቻቸት ባሻገር የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንና የመከላከያ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ…

የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የኮሮና ቫይረስ በሽታን በመከላከል ዙሪያ የሥራ መመሪያ ሰጡ

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ የኮሮና ቫይረስ በሽታን [COVID-19] በስኳር ኢንደስትሪ ለመከላከል የተከናወኑ ሥራዎችን አፈጻጸም ሪፖርት ካዳመጡ በኋላ የሥራ መመሪያ ሰጡ፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ወረርሽኙን በተቀናጀ መልክ ከመከላከል አኳያ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ የሥራ መመሪያ ለመስጠት ዛሬ መጋቢት 30/2012 ዓ.ም. የዋና መ/ቤት የስትሪንግና የቴክኒክ ኮሚቴዎችን እንዲሁም የማኔጅመንት አባላትን በኮርፖሬሽኑ የመሰብሰቢያ አዳራሽ አነጋግረዋል፡፡ በዚሁ ወቅት በስኳር ፋብሪካዎች፣ ፕሮጀክቶችና በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት ወረርሽኙን ለመከላከል የተከናወኑ ሥራዎች አፈጻጸም በስትሪንግ ኮሚቴው ሰብሳቢና የሰርቪስ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታፈሰ አሰፋ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ሪፖርቱን ካዳመጡ በኋላ በስኳር…

የኮሮና ቫይረስ በሽታ [COVID-19] ሥርጭትን ለመከላከል የተከናወኑ ሥራዎች አፈጻጸም ተገመገመ

በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የኮሮና ቫይረስ በሽታ [COVID-19] ሥርጭትን ለመከላከል መጋቢት 8/2012 ዓ.ም በዋና መ/ቤት የተቋቋሙት የስትሪንግና የቴክኒክ ኮሚቴዎች እስከ መጋቢት 25/2012 ዓ.ም ድረስ ያከናወኗቸውን ሥራዎች አፈጻጸም ገመገሙ፡፡ የሁለቱም ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎችና አባላት በተገኙበት በዋና መ/ቤት የስብሰባ አዳራሽ መጋቢት 25/2012 ዓ.ም የተካሄደውን የአፈጻጸም ግምገማ የመሩት የስትሪንግ ኮሚቴው ሰብሳቢና የሰርቪስ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ታፈሰ አሰፋ ናቸው፡፡ የእለቱን ስብሰባ ሲከፍቱ እንደተናገሩት፣ ስትሪንግ ኮሚቴው የቴክኒክ ኮሚቴው ያቀረበውን ዝርዝር ተግባራትና የበጀት ጥያቄ ከመረመረ በኋላ በጀት መመደቡን እንዲሁም ከተለያዩ አካላት በድጋፍ ያገኛቸውንና በግዢ ያሟላቸውን የንፅህና መጠበቂያና የመከላከያ ቁሳቁሶች ለዋና መ/ቤት፣ ለስኳር…

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር የተመራ የልዑካን ቡድን የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክትን ጎበኘ

በአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራና የክልሉን ከፍተኛ አመራሮች እና ባለሃብቶች ያካተተ የልዑካን ቡድን የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የሥራ እንቅስቃሴን መጋቢት 13/2012 ዓ.ም ጎብኝቷል፡፡ በጉብኝቱ ወቅት የጣና በለስ ቁጥር ሶስት ስኳር ፋብሪካ ስለሚገኝበት ሁኔታ እንዲሁም የፋብሪካ ቁጥር አንድ የግንባታ ሂደትና በፕሮጀክቱ እየተካሄደ ስለሚገኘው የአትክልትና ፍራፍሬ ልማት በፕሮጀክቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ በአቶ አንተነህ አሰጌ አማካይነት ለልዑካን ቡደኑ ገለጻ ተደርጓል፡፡ በዚሁ ወቅት ርዕሰ መሰተዳድሩ አቶ ተመስገን ጥሩነህ ባደረጉት ንግግር የፋብሪካ ቁጥር አንድ ግንባታ እንዲፋጠንና ወደ ምርት እንዲገባ የክልሉ መንግሥት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚያደርግ አስታውቀዋል፡፡ በጉብኝቱ የተሳተፉ ባለሃብቶች በበኩላቸው አካባቢው…