ስኳር ኮርፖሬሽን በግብር ክፍያ በፕላቲኒየም ደረጃ እውቅና አገኘ

የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካም በወርቅ ደረጃ እውቅና ተሰጥቶታል በፌደራል ግብር ከፋዮች እውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓት ላይ ስኳር ኮርፖሬሽን በፕላቲኒየም ደረጃ እውቅና አገኘ፡፡ ሽልማቱን የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ መስከረም 7/2013 ዓ.ም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) እጅ ተቀብለዋል፡፡ በተመሳሳይ የፊንጫኣ ስኳር ፋብሪካ በወርቅ ደረጃ እውቅና ከተሰጣቸው ግብር ከፋዮች   መካከል አንዱ ሆኖአል፡፡ በእውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓቱ ላይ 20 ግብር ከፋዮች በፕላቲኒየም ደረጃ፣ 60 ግብር ከፋዮች በወርቅ እንዲሁም 120 ግብር ከፋዮች በብር ደረጃ እውቅና አግኝተዋል። ሁለተኛው ዙር የፌደራል ግብር ከፋዮች የእውቅናና ሽልማት ሥነ ስርዓት በተካሄደበት ወቅት ታማኝ ግብር ከፋዮች በመንግሥት ተቋማት…

የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕከት

ዘመን ዘመንን እየተካ እነሆ ለ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ደርሰናል፡፡ በዘመናት ውስጥ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የስኳር ኢንደስትሪ ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ስኬቶችና ተግዳሮቶች ውስጥ አልፎ ዛሬ ላይ ዘርፉ ሲጀመር ወደሚታወቅበት ዝና ለመመለስ የሚያስችለውን የብሩህ ተስፋ ጉዞ ጀምሯል፡፡ በዚህ ረገድ ኮርፖሬሽናችን የኢንደስትሪውን ህልውና ለማስቀጠል የሚያስችል የአሠራር ማሻሻያ/Reform ቀርጾ ከሐምሌ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመተግበር የዘርፉን ስኬት ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ እውን ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ እነሆ በዚህ መልክ ኢንደስትሪውን ከውድቀት አድኖ በውጤት ለማስቀጠል የተጀመረው ሪፎርም ገና ከጅምሩ ለስኳር የተሻለ ጊዜ እየመጣ መሆኑን አመላክቶአል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይህንንም በ2012 በጀት…

«የስኳር ፕሮጀክቶች እየሰራን እንማራለን በሚል ድፍረት እና ያለ በቂ ገንዘብ መጀመራቸው እንዳይሳኩ አድርጓቸዋል»- አቶ ጋሻው አይችሉህም የስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ስራ አስፈፃሚ

 አዲስ አበባ፡- የስኳር ልማት ፕሮጀክቶች «እየሰራን እንማራለን» በሚል ድፍረትና በቂ የገንዘብ አቅም በሌለበት መጀመራቸው ላለመሳካታቸው ምክንያት እንደሆነ የስኳር ኮርፖሬሽን የኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽን ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ። ሥራ አስፈፃሚው አቶ ጋሻው አይችሉህም በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ እንደተናገሩት፤ ፕሮጀክቶቹ መጠናቀቅም ሆነ መሳካት ያልቻሉት ሲቋቋሙ በቂ የአዋጭነት ጥናት አለመጠናቱ፤ በቂ የገንዘብ አቅም በሌለበት ሁኔታ መጀመራቸው እና ለፋብሪካዎቹ የተመረጡት አካባቢዎች ቆላማ እና ምንም ዓይነት መሠረተ ልማት የሌለባቸው በመሆናቸው ነው። በተጨማሪም የወሰን ማስከበር ችግር፤ ሥራውን የወሰደው ኮንትራክተርም በቂ ልምድ ሳይኖረው «እየሰራን እንማራለን» ብሎ በድፍረት ብቻ ያለ በቂ እውቀት ሥራውን መጀመሩ ለፕሮጀክቶቹ አለመሳካት ዋንኛ ተግዳሮቶች እንደነበር…

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች በአረንጓዴ አሻራ ቀን የራሳቸውን አሻራ አኖሩ

ችግኞችን ሲተክሉ የዘንድሮው ለሰባተኛ ጊዜ ነው   የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባን ጨምሮ የተቋሙ የሥራ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞችና የሠራተኛ ማኅበር ሊቀመንበር በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 5 በሚገኘው ሚሊኒየም ፓርክ ሰኔ 10/2012 ዓ.ም. የጽድ፣ የግራር፣ የወይራ፣ የብሳና፣ የዋንዛ እና ሌሎች የሀገር በቀል እጽዋት ችግኞችን ለሰባተኛ ጊዜ ተክለዋል፡፡   በቀጣይም ችግኞቹ እስኪጸድቁ ድረስ የእንክብካቤ ሥራውን የሚያስተባብር ኮሚቴ ተዋቅሯል፡፡   የኮርፖሬሽኑ የሥራ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በየዓመቱ በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች በሚገኙ ጥብቅ የደን ክልሎች ችግኞችን በመትከል ለአረንጓዴ ልማት እና አካባቢ ጥበቃ የበኩላቸውን አስተዋጽዖ በማበርከት ላይ ናቸው፡፡

በክረምት ወቅት የስኳር ፍላጎት አቅርቦትን ለማሟላት 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ለመጠባበቂያ እየተከማቸ ነው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4 ፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በክረምት ወቅት የስኳር ፍላጎት አቅርቦትን ለማሟላት 3 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ለመጠባበቂያ እየተከማቸ መሆኑ ተገለጸ። የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ከፋና ብሮድካስቲግ ኮርፖሬት ጋር በነበራቸው ቆይታ፥ በተያዘው የ2012 ዓ.ም የክረምት ወቅት የስኳር ፋብሪካዎች ወደ ጥገና መግባትን ተከትሎ እስከ 2013 ጥቅምት ወር በሀገሪቱ የስኳር እጥረት እንዳያጋጥም ዝግጀት መደረጉን ገልጸዋል። በዚህም በሀገር ውስጥ የተመረተ 1 ነጥብ 1 ሚሊየን ኩንታል በመጋዘን የሚገኝ ሲሆን÷ 2 ሚሊየን ኩንታል ስኳር ደግሞ ከውጭ ሀገር በመግዛት በቅርቡ ወደ ሃገር ውስጥ ለማስገባት እየተሰራ ነው ብለዋል። በክርምት ወራት ፋብሪካዎች…

የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተጀመረ

አገር አቀፉን የአረንጓዴ አሻራ ቀን ምክንያት በማድረግ የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሠራተኞችና አመራሮች ግንቦት 28/2012 ዓ.ም የችግኝ ተከላ አካሂደዋል፡፡ የአረንጓዴ አሻራ ቀን የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩን ያስጀመሩት የፋብሪካው ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱልአዚዝ ዩሱፍ ባስተላለፉት መልዕክት የችግኝ ተከላ ለአረንጓዴ ልማት የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ በመሆኑ ችግኝ ከመትከል ባሻገር እንዲጸድቅ መንከባከብ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ከሚደረገው ጥንቃቄ ጋር ተጣጥሞ እንዲካሄድም አስገንዝበዋል፡፡ በእርሻ ኦፕሬሽን ዘርፍ የአገዳ ተከላና እንክብካቤ መመሪያ ሥራ አስኪያጅ ተወካይ አቶ ወርቅነህ አሠፋ በበኩላቸው በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ ቀን መርሃ ግብር በፋብሪካው ከ15 ሺህ በላይ ችግኝ ለመትከል…

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የከሰምና የመተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ጎበኘ

የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ የከሰምና መተሐራ ስኳር ፋብሪካዎችን ግንቦት 13/2012 ዓ.ም በመጎብኘት በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያየ፡፡ በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተርና በስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ አቶ በየነ ገብረመስቀል በተመራው በዚህ ጉብኝትና ውይይት ላይ የስኳር ኮርፖሬሽን የሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሐብታሙ ኃ/ሚካኤል እና የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ ተገኝተዋል፡፡ በወቅቱ በፋብሪካዎቹ ከተካሄደው የመስክ ምልከታ በተጨማሪ የተቋማቱ የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የምርትና ምርታማነት ነባራዊ ሁኔታ እንዲሁም ለምርትና ምርታማነት ማነቆ የሆኑ የፋብሪካ ክፍሎች የመለዋወጫ እጥረትና…

በነባር ስኳር ፋብሪካዎች የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ በኮሮና ቫይረስ መከላከልና በቀጣይ ሥራዎች ዙሪያ በቪድዮ ኮንፈረንስ ውይይት ተካሄደ

በወንጂ ሸዋ፣ በመተሐራና በፊንጫአ ስኳር ፋብሪካዎች የ10 ወራት ዕቅድ አፈጻጸም፣ የፋብሪካ የክረምት ጥገናና የዝግጅት ምዕራፍ ዕቅድ እንዲሁም በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙሪያ ግንቦት 4/2012 ዓ.ም በቪድዮ ኮንፈረንስ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ወዮ ሮባ በተመራው በዚህ ውይይት ላይ የኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት አመራሮች እንዲሁም የሦስቱም ስኳር ፋብሪካዎች ዋና ሥራ አስኪያጆችና የሥራ ኃላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡ በውይይቱ ወቅት የፋብሪካዎቹ ሦስተኛ ሩብ ዓመት የምርት አፈጻጸም ካለፈው በጀት ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር አበረታች መሆኑን የገለጹት የኮርፖሬሽኑ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ ይሁንና ከዘንድሮ ዕቅድ አኳያ ሲታይ ግን የሚቀረውን ለማሟላት በቀጣይ ጊዜያት ትኩረት ሰጥቶ መረባረብ…

ስኳር ኮርፖሬሽን 100 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን በእርዳታ አገኘ

ስኳር ኮርፖሬሽን 100 ሺህ የአፍ መሸፈኛ ጭምብሎችን/Face masks የኦሞ ኩራዝ ቁጥር 5 ስኳር ፋብሪካን ከሚገነባው የቻይናው JIEC ኩባንያ (Jiang Lian International Engineering Company) በእርዳታ አገኘ፡፡ በእርዳታ የተገኙትን ጭምብሎች ለስኳር ፋብሪካዎች፣ ፕሮጀክቶችና ለኮርፖሬሽኑ ዋና መ/ቤት ማከፋፈል ተጀምሯል፡፡ ይህም እርዳታ በስኳር ኢንደስትሪ የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ጥረት ያግዛል፡፡

በስኳር ኢንደስትሪ የኮሮና ቫይረስን/COVID-19 ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል

በስኳር ኢንደስትሪ የኮሮና ቫይረስ በሽታን/COVID-19 ለመከላከል የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ በስኳር ኮርፖሬሽን ዋና መ/ቤት፣ በስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች በተቋቋሙ አብይና የቴክኒክ ኮሚቴዎች መሪነት ወረርሽኙን ለመከላከል ሰፊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ይገኛል፡፡ በተለይም በርካታ ሠራተኞች በሚገኙባቸው የስኳር ፋብሪካዎችና ፕሮጀክቶች የቫይረሱን ሥርጭት በተቀናጀ ሁኔታ ለመከላከል እንዲቻል በአካባቢዎቹ ከሚገኙ ማኅበረሰቦች፣ አጋር የልማት ድርጅቶች እንዲሁም ከወረዳ መስተዳድሮች ጋር ጥምረት በመፍጠር ሥራዎችን በጋራ ለመፈጸም የሚያስችሉ እንቅስቃሴዎች በመደረግ ላይ ናቸው፡፡ ስኳር ኮርፖሬሽን ከጤና ሚኒስቴር፣ ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እንዲሁም መንግሥታዊና መንግሥታዊ ካልሆኑ የጤና ተቋማት ጋር በፈጠረው ግንኙነት ለጤና ባለሙያዎች ሥልጠናዎችን ከማመቻቸት ባሻገር የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችንና የመከላከያ ግብዓቶችን ለማሰባሰብ…