የስኳር ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ የአዲስ ዓመት የእንኳን አደረሳችሁ መልዕከት

ዘመን ዘመንን እየተካ እነሆ ለ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ አዲስ ዓመት ደርሰናል፡፡ በዘመናት ውስጥ ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ዕድሜን ያስቆጠረው የኢትዮጵያ የስኳር ኢንደስትሪ ባለፉት 65 ዓመታት በበርካታ ስኬቶችና ተግዳሮቶች ውስጥ አልፎ ዛሬ ላይ ዘርፉ ሲጀመር ወደሚታወቅበት ዝና ለመመለስ የሚያስችለውን የብሩህ ተስፋ ጉዞ ጀምሯል፡፡ በዚህ ረገድ ኮርፖሬሽናችን የኢንደስትሪውን ህልውና ለማስቀጠል የሚያስችል የአሠራር ማሻሻያ/Reform ቀርጾ ከሐምሌ 2011 ዓ.ም ጀምሮ በመተግበር የዘርፉን ስኬት ሩቅ በማይባል ጊዜ ውስጥ እውን ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ እነሆ በዚህ መልክ ኢንደስትሪውን ከውድቀት አድኖ በውጤት ለማስቀጠል የተጀመረው ሪፎርም ገና ከጅምሩ ለስኳር የተሻለ ጊዜ እየመጣ መሆኑን አመላክቶአል ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡ ይህንንም በ2012 በጀት…

ምርምርና ልማት ዋና ማዕከል

በሀገራችን በስኳር ኢንዱስትሪ የምርምር ሥራ የተጀመረው ኤች.ቪ.ኤ በተባለ የሆላንድ ኩባንያ እ.ኤ.አ. በ1951 ነበር። የምርምር ክፍሉ ዋናው ማዕከል በአምስተርዳም ሆኖ በወቅቱ በኢትዮጵያ ለሚገኙ የስኳር ፋብሪካዎች ጠንካራ ድጋፍ ይሰጥ ነበር፡፡ ኩባንያው በወንጂ ሸንኮራ አገዳ መትከልና ስኳር ማምረት ሲጀምር እ.ኤ.አ. ከ1958 አንስቶ በስኳር ኢንዱስትሪ ሥልጠና ይሰጥ እንደነበር መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡ ኋላ ላይ የፋብሪካዎቹን ወደ መንግሥት ይዞታነት መሸጋገር ተከትሎ የምርምር ሥራው በተለያዩ አደረጃጀቶች ሲመራ ቆይቶ የስኳር ኮርፖሬሽን በአዋጅ ቁጥር 192/2003 ሲቋቋም ለምርምርና ሥልጠና ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶት የሚከተሉትን አበይት ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ምርትና ምርታማነትን ማሳደግና የማምረቻ ወጪን መቀነስ የሚያስችል እንዲሁም ችግር ፈቺነትን መሰረት ያደረገ ምርምር (applied…

ምርቶች

የሀገራችን ተሞክሮ በስኳር ተጓዳኝ ምርቶች (Sugar Co-products)  የኤሌክትሪክ ኃይል (Electricity) ፍራፍሬ (Fruits) ; Orange, Banana, Mango የእንስሳት መኖ (Animal feed) ከብት ማድለብ (Cattle Fattening) ጥጥ (Cotton) ሩዝ (Rice) አኩሪ አተር (Soya bean) ሰሊጥ (Sesame) ስንዴ (Wheat) ቦሎቄ (Haricot bean) ማሾ (Mung bean) የስኳር ዋንኛ ተረፈ ምርቶች (Major Sugar By-products) ሞላሰስ (Molasses) ኢታኖል (Ethanol) ባጋስ (Bagasse)

ፕሮጀክቶች

ኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት የኦሞ ኩራዝ ስኳር ልማት ፕሮጀክት በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በደቡብ ኦሞ ዞን (ሰላማጎ እና ኛንጋቶም ወረዳዎች)፣ በቤንች ማጂ ዞን (ሱርማ እና ሜኢኒትሻሻ ወረዳዎች) እና በካፋ ዞን (ዴቻ ወረዳ) የተመረጡ አካባቢዎች እየተካሄደ የሚገኝ ግዙፍ ፕሮጀክት ነው፡፡ በፕሮጀክቱ ስር እየተገነቡ ከሚገኙ አራት የስኳር ፋብሪካዎች በተሽከርካሪ ለመድረስ ከአዲስ አበባ በሆሳዕና – አርባ ምንጭ – ጂንካ መስመር ከ825-954 ኪሎ ሜትር ወይም ከአዲስ አበባ በሻሸመኔ – አርባ ምንጭ – ጂንካ መንገድ ከ859-988 ኪሎ ሜትር መጓዝን ይጠይቃል፡፡ በአየር ትራንስፖርት ከሆነ ደግሞ ከአዲስ አበባ ጂንካ ለአንድ ሰዓት ያህል በመብረር ከጂንካ ፋብሪካዎቹ ያሉበት ድረስ ከ80-220…